አዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት
Addis Ababa Media Council.
/
በአርሲ የኦርቶዶክሳዊያንን እና በጎንደር የሕጻናትን አጥብቀን እናወግዛለን !!!

ጥቅምት 11፣ 2019

የኢትዮጲያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ትኩረት በሰሜን ኢትዮጲያ ባለው ጦርነት ላይ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር ፣ አርሲ ዞን፣ መንግሥታዊ መዋቅሮች መሪ ተዋናዮች በሆኑበት ሁኔታ የኦርቶዶክስ እምነት ተከተዮችን የማጽዳት ዘመቻው ዳግም አገርሽቷል ።

በአርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በእምነታቸው እየተለዩ በግፍ መገደላቸውን፣ ንብረታቸው መዘረፉን አና ገሚሶቹም መታገታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም በአርሲ ዞን፣ በሺርካ ወረዳ፣ ጌቱ አሰፋ የተባሉ ግለሰብ የእርሻ ሥራ ላይ እያሉ የተገደሉ ሲሆን፣ 50 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው በታጣቂዎች ተወስደው ታግተዋል።በዚያው ወረዳ በዘንባባ ቀበሌ ዘውዴ ሃብቴ እና አስራሱ ተስፋዬ በግፍ የተገደሉ ሲሆን፣ በተጨማሪም
ፍርዴ አሰፋ፣ ገናና አሰፋ፣ እፋ ዘነበ፣ አስናቀ ዘውዴ፣ ወጋየሁ መርሻ የተባሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል።

በሌላ በኩል፣ በአርሲ ዞን፣ ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ በወርሃ ​ጥቅምት 5፣ 2019 ዓ.ም ዘነባ ነጋሽ፣ ሳሙኤል ዋሌ፣ ብሩህ አበራ የተባሉ ኦርቶዶክሳዊያን በግፍ ተገድለዋል።
በአርሲ ዞን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከ600 በላይ ኦርቶዶክሳዊያን እምነት ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ የ101 አመት እድሜ ያለውን ቤተክርስቲያንን ጨምሮ በርካታ አቢያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት ይህንን ተከታታይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ለይቶ እና መርጦ የማጽዳት ዘመቻ በጥብቅ ያወግዛል። የዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህን ጉዳይ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለው ጥሪ ያቀርባል።

በሌላ በኩል፣ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ ም አገዛዙ በደቡብ ጎንደር፣ በወሎ ቤተ አምሃራ ሳይንት እና በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በሲቪሊያን ላይ ያነጣጠረ ከፍተኛ የድሮን ድብደባ በመፈጸም በርካታ ንጹሃንን በግፍ ጨፍጭፏል።

በደቡብ ጎንደር፣ ደራ ወረዳ፣ በሰና ቀበሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ማክሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4:45 ደቂቃ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ህይወታቸው እንዳለፈ ሌሎች ደግሞ ቀላል እና ከባድ የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ለማወቅ ተችሏል።

ማክሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2019 አገዛዙ በወሎ/ቤተአምሃራ፣ በአማራ ሳይንት፣ በዳንሳ ወረዳ ቀበሌ 01 በሚገኘው በአቢሲኒያ ባንክ እና አማራ ባንክ ተቋማት ላይ ባደረገው የድሮን ድብደባ፣ በርካታ ንጹሃን መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ማወቅ ተችሏል።

በደቡብ ጎንደር፣ ደራ ወረዳ፣ ሰና ቀበሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተደረገው የድሮን ድብደባ፣ እድሜያቸው ከ 5-15 የሚሆኑ ታዳጊ ህጻናት ያሉበት ትምህርት ቤት ላይ የተደረገ ወታደራዊ ጥቃት እንደመሆኑ መጠን፣ እንዲሁም በወሎ/ቤተአማራ በሲቨል ተቋማት ላይ የተፈፀመ ወታደራዊ ጥቃት በመሆኑ አገዛዙ ዓለም አቀፍ የጦርነት ሕግ እና ደንብ በመጣስ የጦር ወንጀል ፈፅሟል። ይህን አረመኔያዊ ድርጊት በጥብቅ እያወገዝን፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህንንም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው እና እርምጃ እንዲወስድ እንማፀናለን።

ስንተባበር እንጠንክራለን፣ እናሸንፋለን !!!

የአዲስ አበባ ሚዲያ ምክር ቤት፣
ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ ም።